HealthFlex
×
  • Home
  • who we are
  • What We Do
    • Providing Trainings
    • Consultancy Services
    • Catering & Lodging Service
    • Training Facility
      • Big Conference Room
      • Medium Hall
      • Syndicate Room
      • Training Room I
      • Training Room 2
      • Training Room 3
    • Fitness & Wellness Service
  • Announcements & Publication
    • Training Catalogue
    • Call for training
    • Gallery
  • Book Now
  • Contact us

ማኅበሩ ለግጭት ተጎጂዎች የቅርብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ

September 1, 2021Uncategorized

ከማኅበሩ ቅርንጫፎች በተገኘ መረጃ በሰሜን ጎንደር ደባርቅ 15 ሺህ፣ በደቡብ ወሎ ደሴ ላይ 110 ሺህ እንዲሁም በዋግምራ ከ20 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች በአጠቃላይ 23 አምቡላንሶችን በማሰማራት 1500 ለሚሆኑ ተጎጂወች የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና እርዳታ እና ፅኑ ህሙማንን ወደ ጤና ተቋማት የማድረስ ሰብዓዊ ተግባር ተከናውኗል፡፡

በሰሜን ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች 13 እንዲሁም በደቡብ ወሎ 4 ድንኳኖችን በመትከል ለተፈናቃይ ወገኖቻችን ጊዜያዊ መጠለያ እንዲያገኙ ጥረት ተደርጓል፡፡ ለተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ይዘት ያላቸውን ብስኩቶች፣ የማብሰያ እና ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ አልባሳት ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡

ግጭቶች ባሉባቸው ቦታዎች የጤና ተቋማት ላይ እየደረሰ በሚገኘው የሥራ ጫና ምክንያት የመድኃኒት እና ሌሎችም ለተቋማቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እጥረት ድጋፍ ይሻሉ፡፡ ማኅበሩ በዚህ በኩል ለጎንደር ከተማ፣ ለጭልጋ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ደሴ፣ ሀይቅ፣ ኮምቦልቻ፣ ዳንግላ ፣መራዊ እና አዴት ለሚገኙ የጤና ተቋማት የማደንዘዣ መድኃኒት/ Anesthesia/ ጨምሮ ልዩ ልዩ መሰረታዊ መድኃኒቶች፣ዊልቼር፣ የህክምና አልባሳት እና የመኝታ ቁሳቁሶች አበርክቷል፡፡ በአጠቃላው በደቡብ ጎንደርና በደቡብ ወሎ ለ 20 ሺኅ ተረጂዎች ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር ማህበሩ ዕርዳታ አድርጓል፡፡

በቅርቡ በአማራ ክልል ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን፣ ሰሜን ጎንደር እና ዋግምህራ አካባቢዎች የአምቡላንስ እና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና እርዳታ፣ የምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ መሰረታዊ የሆኑ መድኃኒቶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር ለ12 ሺህ ተፈናቃዮች ደሴ ላይ እርዳታ በማደል ላይ ይገኛል፡፡ ተመሳሳይ እርዳታም ለደቡብ ጎንደር ተፈናቃዮች በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

ህብረተሰቡም እንደተለመደው በቆይታ ግዜ ሊበላሹ የማይችሉ ምግቦች፣ አልባሳት፣ የመመገቢያ እና ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና ሌሎችም ድጋፎችን ስታዲዮም አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት እና አቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የማኅበሩ ቅርንጫፎች በመሄድ ትብብር እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡

የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተጠቀሰው የማኅበሩን የኢተዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

                                                                                              ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 000000 902 008

Add Comment Cancel


Recent Posts

  • Hello world!
  • “በአለም አቀፍ ደረጃ የርሃብ አደጋ በአስከፊ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል” – የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ቀይ ጨረቃ ንቅናቄ
  • The Ethiopian Red Cross Society is evacuating residents at risk of flooding in the Afar region
  • Five districts of the Afar region suspected of flooding
  • Society receives vehicles worth more than Birr 70 million

Recent Comments

  1. A WordPress Commenter on Hello world!

Contact Us

Ethiopian Red Cross Society-Training Institute, Nifas Silk Lafto Sub City, Woreda 10, Debrezite Road, 400 meter right to Aday Ababa Textile & Garment Factory.

+251-11-442-02-35

ERCS-TI@redcrosseth.org

Ethiopian Red Cross Society Triaining Institute

Quick Links

  • Book a Training Room
  • Register for Training
  • Book Now
  • Call for training
  • Providing Trainings
  • Training Catalogue
  • Facebook
  • YouTube
  • X
  • Telegram
  • Flickr
Copyright ©2026 | All Rights Reserved
Designed and Developed By Rackmint System